La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ታንኳዎቹንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ፣ ሁሉን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ ሁሉን ነገር ትተው የኢየሱስ ተከታዮች ሆኑ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ታን​ኳ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር አወ​ጡና ሁሉን ትተው ተከ​ተ​ሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo



ሉቃስ 5:11
11 Referencias Cruzadas  

ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ “እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ የምናገኘው ታዲያ ምንድነው?” አለው።


ማንም ስለ ስሜ ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘለዓለም ሕይወትንም ይወርሳል።


ወዲያውኑ መረባቸውን ጥለው ተከተሉት።


እነርሱም ወዲያውኑ ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።


ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ “እንግዲያው አንድ ነገር ይጐድልሃል፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሽጥ፤ ለድኾችም ስጥ፤ በሰማይ የተከማቸ ሀብት ታገኛለህ፤ ከዚያ በኋላና፤ ተከተለኝም” አለው።


እርሱም ሁሉንም ነገር ትቶ፤ ተነሥቶ ተከተለው።