La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፣ “እኔ በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ ጲላጦስ ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡም “በዚህ ሰው ምንም በደል አላገኘሁበትም” አለ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጲላ​ጦ​ስም ለካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ድስ እንኳ በደል የለም” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፦ በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም አለ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 23:4
13 Referencias Cruzadas  

እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ፥ ሚስቱ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ ጻድቅ ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።


ጲላጦስም፥ “ለምን? ምን የፈጸመው ወንጀል አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን፥ “ስቀለው” እያሉ የባሰ ጮኹ።


ለሦስተኛ ጊዜም “ይህ ሰው ምን ክፉ ነገር ሠራ? ለሞት የሚያደርሰው በደል አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ፤” አላቸው።


ጲላጦስ “እውነት ምንድነው?” አለው። ይህንንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጣና “እኔስ አንዲት በደል እንኳን አላገኘሁበትም።


እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፤ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቆረጥሁ።


የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቆርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው።


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


ነገር ግን ነውርና እድፍ እንደሌለው በግ ደም፥ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው፥


እርሱ ኃጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም፤


ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።