“አንተ የአሁድ ንጉሥ ከሆንህ፥ ራስህን አድን፤” እያሉ ይቀልዱበት ነበር።
“አንተ የአይሁድ ንጉሥ ከሆንህ፣ ራስህን አድን” ይሉት ነበር።
እንዲሁም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ከሆንክ እስቲ ራስህን አድን!” ይሉት ነበር።
እንዲህም ይሉት ነበር፥ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ከሆንህስ ራስህን አድን።”
አንተስ የአሁድ ንጉሥ ከሆንህ፥ ራስህን አድን እያሉ ይዘብቱበት ነበር።
“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ነው፤ አሁን ከመስቀል ይውረድና እኛም በእርሱ እናምናለን።
በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሏልና የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው።”
የክሱ ጽሑፍም፥ “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ነበር።
ከተሰቀሉት ክፉ አድራጊዎችም አንዱ “አንተ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን፤” ብሎ ሰደበው።