La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁሉም በአንድነት “ይህን አስወግደው፤ በርባንንም ፍታልን፤” እያሉ ጮኹ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ላይ፣ “ይህን ሰው ወዲያ አስወግደው! በርባንን ፍታልን!” እያሉ ጮኹ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ “ይህን ሰው አስወግደው! በርባንን ግን ፍታልን!” እያሉ በአንድ ድምፅ ጮኹ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁሉም በሙሉ፥ “ይህን አስ​ወ​ግ​ደው፥ ስቀ​ለ​ውም፥ በር​ባ​ንን ግን ፍታ​ልን” ብለው ጮሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁላቸውም በአንድነት፦ ይህን አስወግድ፥ በርባንንም ፍታልን እያሉ ጮኹ፤

Ver Capítulo



ሉቃስ 23:18
10 Referencias Cruzadas  

(በበዓሉ አንድ እስረኛ ለሕዝቡ ይፈታላቸው ዘንድ ግድ ነበረና።)


እርሱም ሁከትን በከተማ አስነሥቶ ሰውን ስለ ገደለ በወኅኒ ታስሮ ነበር።


ጴጥሮስ ግን በውጭ በበሩ ቆሞ ነበር። በሊቀ ካህናቱም ዘንድ የታወቀው ሌላው ደቀመዝሙር ወጣ፤ ለበረኛይቱም ነግሮ ጴጥሮስን አስገባው።


ብዙ ሕዝብ “አስወግደው!” እያሉና እየጮኹ ይከተሉ ነበርና።


እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።


እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፤