ሉቃስ 20:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠንቀቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ “ዘርፋፋ ቀሚስ ለብሰው መዞርን፣ በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታን፣ በምኵራብ የከበሬታ መቀመጫን፣ በግብዣ ቦታም የክብር ስፍራን ይፈልጋሉና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ረጃጅም ልብስ ለብሰው ወዲያና ወዲህ መዞርን፥ በገበያም የክብር ሰላምታ መቀበልን፥ በምኲራብ የክብር ወንበርን፥ በግብዣም የክብር ስፍራን ከሚወዱ ከሕግ መምህራን ተጠንቀቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ልብሳቸውን አንዘርፍፈው ወዲያ ወዲህ ማለትን ከሚሹ፥ በገበያ እጅ መነሣትንና በአደባባይ ፊት ለፊት፥ በማዕድም ጊዜ በከበሬታ መቀመጫ መቀመጥን ከሚወዱ ጻፎች ተጠበቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤ |
በዚያን ጊዜ፥ በሺዎች የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ከብዛታቸው የተነሣ እየተረጋገጡ ሳለ፥ በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ እርሱም ግብዝነት ነው።