Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 20:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 የመበለቶችን ቤት የሚበሉ፥ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ ናቸው፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 በረዥም ጸሎታቸው እያሳበቡ የመበለቶችን ቤት ያራቍታሉ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 እነርሱም ለታይታ በሚያቀርቡት ረጅም ጸሎት እያመካኙ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ይበዘብዛሉ፤ ስለዚህ እነርሱን የባሰ ፍርድ ያገኛቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 የመ​በ​ለ​ቶ​ችን ገን​ዘብ የሚ​በሉ፥ ለም​ክ​ን​ያት ጸሎ​ት​ንም የሚ​ያ​ስ​ረ​ዝሙ እነ​ዚህ ታላቅ ፍር​ድን ይቀ​በ​ላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ፥ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ አለ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 20:47
23 Referencias Cruzadas  

በረጅም ጸሎታቸው እያሳበቡ የመበለቶችን ቤት ያራቁታሉ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”


ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ፤ ምክንያቱም አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁ።


እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ በግልጥ ይናገራሉ ዳሩ ግን በሥራቸው ይክዱታል፤ የሚያጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ ብቁ ያልሆኑ ናቸው።


በዚያን ጊዜ፥ በሺዎች የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ከብዛታቸው የተነሣ እየተረጋገጡ ሳለ፥ በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ እርሱም ግብዝነት ነው።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


መልካሙን የምትጠሉ፥ ክፉውን የምትወዱ፤ ቁርበታቸውን ከላያቸው ላይ ገፈፋችሁ፥ ሥጋቸውንም ከአጥንታቸው ለያያችሁ፤


ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሕዝቤ እንደ ጠላት ሆኖ ተነሥቶአል፤ በሰላም ሳይፈሩ የሚያልፉትን ቀሚስንና መጐናጸፊያን ገፈፋችሁ፥ ከሰልፍ እንደሚመለሱ አደረጋችኋቸው።


የድሆችን ራስ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ የትሑታንንም መንገድ ያጣምማሉ፤ ቅዱሱንም ስሜን ለማርከስ አባትና ልጅ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፤


ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።


የድኾችን መብት ለሚገፉ፤ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፤ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፤ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!


እንደምታውቁት፥ የቁልምጫን ቃል ለስግብግብነትም ማመካኛ የሚሆን ነገር ከቶ አልተገኘብንም፥ እግዚአብሔርም ምስክር ነው።


የእርሻ ቦታዎችን ይመኛሉ፥ ይይዟቸዋልም፤ ቤቶችንም፥ ይወስዷቸዋልም፤ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ውርሱን ይጨቁናሉ።


አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ መጻተኛውን ጨቆኑ፥ በአንቺ ውስጥ የሙት ልጅንና መበለቲቱን አስጨነቁ።


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።


“ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ፥ በገበያም ሰላምታ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠንቀቁ፤


ዐይኑንም አንሥቶ በምጽዋት መቀበያ መባቸውን የሚያስቀምጡ ሀብታሞችን አየ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios