La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 19:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ በታላቅ ትኩረት ይሰሙት ነበርና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከርሱ ጋራ ተቈራኝተው ትምህርቱን ይከታተሉ ስለ ነበር፣ የሚያደርጉት ግራ ገባቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት በመፈለግ ልባቸው ተማርኮ ስለ ነበረ ሊገድሉት የፈለጉት ወገኖች ምንም ማድረግ አልቻሉም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ትም​ህ​ር​ቱን በመ​ስ​ማት ይመ​ሰጡ ነበ​ርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ሲሰሙት ተንጠልጥለውበት ነበርና።

Ver Capítulo



ሉቃስ 19:48
8 Referencias Cruzadas  

በውኃው በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ ወንዶች፥ ሴቶች፥ የሚያስተውሉም ባሉበት፥ ከማለዳ ጀመሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ በጽሞና ያደምጥ ነበር።


በየዕለቱም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች የሕዝቡ መሪዎችም ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፤


አንድ ቀንም ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ወንጌልንም ሲሰብክላቸው፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ ቀረቡና


ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ ያሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።