ሉቃስ 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጀመሪያውም ደርሶ ‘ጌታ ሆይ! ምናንህ ዐሥር ምናን አተረፈ፤’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የመጀመሪያው አገልጋይ ቀርቦ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ የሰጠኸኝ ምናን ዐሥር ምናን ትርፍ አስገኝቷል’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው አገልጋይ ቀርቦ፦ ‘ጌታ ሆይ! የሰጠኸኝ አንድ ምናን እነሆ፥ ዐሥር ምናን አትርፎአል’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደኛውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምናንህ ዐሥር ነበር፤ እነሆ ዐሥር ምናን አትርፌአለሁ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛውም ደርሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው። |
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።