እነርሱ ግን ዝም አሉ። ይዞም ፈወሰውና አሰናበተው።
እነርሱ ግን ዝም አሉ። እርሱም ሰውየውን ይዞ ፈወሰውና አሰናበተው።
እነርሱ ግን ምንም ሳይመልሱ ዝም አሉ፤ ኢየሱስ የታመመውን ሰው ይዞ ፈወሰውና አሰናበተው።
እነርሱም ዝም አሉ፤ ይዞም ፈወሰውና ሰደደው።
አንድም ቃል እንኳ ሊመልስለት የቻለ ማንም አልነበረም፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ አንድስ እንኳ አልነበረም።
ኢየሱስም መልሶ “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም?” ብሎ ሕግ አዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን ጠየቀ።
“ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጉድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው።