La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 12:58 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ለመታረቅ ትጋ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከባላጋራህ ጋራ ወደ ዳኛ ፊት ለመቅረብ ስትሄድ፣ ገና በመንገድ ላይ ሳለህ ለመታረቅ ጥረት አድርግ፤ አለዚያ ጐትቶ ወደ ዳኛው ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለመኰንኑ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኰንኑም ወደ ወህኒ ይጥልሃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ባላጋራህ ከሶህ ወደ ፍርድ ቤት በሚወስድህ ጊዜ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ለመስማማት ተጣጣር፤ አለበለዚያ እርሱ ወደ ዳኛ ጐትቶ ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አሳሪውም ወደ እስር ቤት ያገባሃል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከባ​ለ​ጋ​ራህ ጋር ወደ ሹም በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ ወደ ዳኛ እን​ዳ​ይ​ወ​ስ​ድህ በመ​ን​ገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳ​ህ​ንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎ​ሌው አሳ​ልፎ ይሰ​ጥ​ሃ​ልና። ሎሌ​ውም በወ​ኅኒ ቤት ያስ​ር​ሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ እንድትታረቅ ትጋ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 12:58
20 Referencias Cruzadas  

“እንግዲህ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም መልካምን ታገኛለህ።


የሚከራከረው ቅን ሰው መሆኑን ይመሰክር ነበር፥ እኔም በፈራጅ ፊት ለዘለዓለም ነፃ እወጣ ነበር።”


ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል፥ ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም።


እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፥ አለዚያ ግን ስበታትናችሁ የሚያድንም የለም።


ጌታ በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤


እርሱ ግን አልፈለገም፤ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ ሄዶ በወኅኒ አሳሰረው።


እርሱ፥ “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፤” ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳንም ቀን አሁን ነው።


በዚያው መንፈስ በእስር ቤት ወዳሉት ነፍሳት ሄዶ ሰበከላቸው፤


ከመለየቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች፥ በየትኛውም ጊዜ ማሰብ ትችሉ ዘንድ፥ በብርቱ እተጋለሁ።


ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱሳን ሁሉ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ እንድመክራችሁና እንድጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።


ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤