La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 12:57 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“እናንተ ራሳችሁ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ለምን አትፈርዱም?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ታዲያ ራሳችሁ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ለምን አትፈርዱም?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ስለምን እናንተ ራሳችሁ ትክክለኛውን ነገር ዐውቃችሁ አትፈርዱም?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ ራሳ​ችሁ እው​ነ​ቱን ለምን አት​ፈ​ር​ዱም?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ራሳችሁ ደግሞ ጽድቅን የማትፈርዱ ስለ ምን ነው?

Ver Capítulo



ሉቃስ 12:57
10 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ፥ በበለሲቱ ዛፍ እንደተደረገው ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት ይሆናል፤


ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበር፥ አላመናችሁትም፤ ቀራጮችና ዘማውያን ግን አመኑት፤ በመጨረሻም ይህንን አይታችሁ እንኳ ልታምኑት ንስሐ አልገባችሁም።


ሲያቈጠቁጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።


ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።”


በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ፤” ብሎ መከራቸው።


በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትከናነብ ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን?


ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?


አስተዋዮች ቢሆኑ፥ ይህንን በተገነዘቡ፥ ፍጻሜያቸውንም ባሰቡ ነበር!