እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ ‘ጌታን እወቅ’ ብሎ ከእንግዲህ ወዲህ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል ጌታ። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስምና።”
ሉቃስ 1:77 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በኀጢአታቸው ስርየት የመዳንን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኀጢአታቸውን ስርየት ከማግኘታቸው የተነሣ፤ ለሕዝቡ የመዳንን ዕውቀት ትሰጥ ዘንድ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታም ኃጢአታቸውን ይቅር በማለት የመዳንን ዕውቀት ይሰጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ መድኀኒታቸውን እንዲያውቁ ለአሕዛብ ትሰጣቸው ዘንድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤ |
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ ‘ጌታን እወቅ’ ብሎ ከእንግዲህ ወዲህ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል ጌታ። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስምና።”
እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኀጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፤ ተመለሱም።
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤