La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኤልሳቤጥም መካን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤልሳቤጥ መኻን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ደግሞ ሁለቱም በጣም አርጅተው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።

Ver Capítulo



ሉቃስ 1:7
16 Referencias Cruzadas  

አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ፦ “የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”


አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፥ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር።


ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርሷ ወደ ጌታ ጸለየ፤ ጌታም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤


ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት፥ ያዕቆብንም፦ ልጆች ስጠኝ፥ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው።


ንጉሡ ዳዊትም ዕድሜው ገፍቶ ስለ ሸመገለ፥ ልብስ ደራርበው ቢያለብሱትም ሙቀት ሊሰጠው አልቻለም ነበር።


ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባሏም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ።


በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ሴት ልጆች ወገን ነበረች፤ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ በጌታ ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ ይመላለሱ ነበር።


እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት በክህነት ሲያገለግል፥


መቶ ዓመት ሆኖት ሳለ ምውት የሆነውን የራሱን አካልና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆን አስቦ በእምነት አልደከመም፤


ሣራም ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደሆነ ስለ ቈጠረች፥ ምንም እንኳን መካን ብትሆን፥ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች።


እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም አንዲቱ ሐና፥ ሁለተኛዪቱም ጵኒና ነበር። ጵኒና ልጆች ነበሯት፤ ሐና ግን ምንም ልጅ አልነበራትም።