Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ኤልሳቤጥ መኻን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ደግሞ ሁለቱም በጣም አርጅተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ኤልሳቤጥም መካን ስለ ነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 1:7
16 Referencias Cruzadas  

ሣራም ተስፋ የሰጣት እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑን ስላወቀች ምንም እንኳ በዕድሜ በመግፋቷ መውለድ የማትችል ብትሆን የመፅነስን ኀይል ያገኘችው በእምነት ነው።


ሕልቃናም ሐናና ፍኒና ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ፍኒና ልጆች ነበሩአት፤ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም፤


አብርሃምና ሣራ በዕድሜአቸው መግፋት አርጅተው ነበር፤ የሣራም፥ ልጅ የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ ነበር።


ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርስዋ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤


ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ።


አብርሃም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ ነገር ግን “ዕድሜው መቶ ዓመት የሆነው ሰው ልጅ መውለድ ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመትዋ ልጅ ልትወልድ ትችላለችን?” ብሎ በማሰብ ሳቀ፤


ዕድሜው መቶ ዓመት ያኽል ስለ ነበረ በሥጋው መድከም እንደ ሞተ በመሆን ምክንያት መውለድ እንደማይችልና ሣራም መኻንና ያረጀች በመሆንዋ መውለድ እንደማትችል ቢያውቅም በእምነቱ ደካማ አልሆነም።


ንጉሥ ዳዊት እጅግ ሸምግሎ ስለ ነበር አገልጋዮቹ የብርድ መከላከያ የሚሆን ልብስ ደራርበው ቢያለብሱትም ሙቀት ሊሰጠው አልቻለም ነበር።


ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ ለመውለድ አለመቻሏን ባወቀች ጊዜ በእኅቷ ቀናችባት፤ ስለዚህ ያዕቆብን “ልጅ ስጠኝ፤ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።


ሄሮድስ በይሁዳ ምድር ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ ከአብያ የክህነት አገልግሎት ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር። እርሱም ከአሮን ዘር የምትወለድ ኤልሳቤጥ የምትባል ሚስት ነበረችው።


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ የጌታንም ትእዛዝና ሥርዓት ያለ ነቀፋ ይጠብቁ ነበር።


በዚያን ጊዜ የዘካርያስ የክህነት ቡድን ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ተረኛ ነበር፤ ስለዚህ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት የክህነቱን አገልግሎት በመፈጸም ላይ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios