ሉቃስ 1:68 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፤ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤ መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቷልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝቡን በምሕረት ስለ ጐበኘና ስላዳነ፥ የእስራኤል አምላክ፥ ጌታ ይመስገን! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤ |
እንዲህም አለ፦ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።”
እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦
ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት ጌታን ባረከ፤ ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ተባረክ።
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።
አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን በምድር ላይ ይጨፈልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም በድንጋይ ላይ የሚኖር ድንጋይ አያስቀሩም፤ የተጐብኘሽበትን ዘመን አላወቅሽምና።”
ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸው፤ እግዚአብሔርንም እንዲህ እያሉ አመሰገኑ፦ “ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል!” “እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጐብኝቶአል!”
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤