አሮንም ሙሴን፦ “እነሆ፥ ዛሬ የኃጢአታቸውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውን በጌታ ፊት አቀረቡ፤ ሆኖም ይህ ሁሉ ነገር በእኔ ላይ ደረሰብኝ፤ ዛሬስ የኃጢአት መሥዋዕት ብበላ ኖሮ በጌታ ፊት መልካም ይሆን ነበርን?” አለው።
ዘሌዋውያን 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ አሮን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዐረደ፤ ልጆቹ ደሙን አቀበሉት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውንም እንስሳ ዐረደ፤ ልጆቹም ደሙን ወደ እርሱ አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፤ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው። |
አሮንም ሙሴን፦ “እነሆ፥ ዛሬ የኃጢአታቸውን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውን በጌታ ፊት አቀረቡ፤ ሆኖም ይህ ሁሉ ነገር በእኔ ላይ ደረሰብኝ፤ ዛሬስ የኃጢአት መሥዋዕት ብበላ ኖሮ በጌታ ፊት መልካም ይሆን ነበርን?” አለው።
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።