ዘሌዋውያን 8:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ፊት ካለው እርሾ ያልነካው ቂጣ ከሚቀመጥበት መሶብ አንድ እርሾ ያልገባበት የቂጣ እንጐቻ፥ አንድም ከዘይት ጋራ የተሰናዳ የቂጣ እንጐቻ፥ አንድም ስስ ቂጣ ወስዶ በስቡና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔርም ፊት ካለው፣ ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ካለበት መሶብ ላይ አንድ ኅብስት፣ አንድ በዘይት የተጋገረ ቂጣ እንዲሁም ስስ ቂጣ ወስዶ በሥቦቹና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፊት ካለው እርሾ ያልነካው ቂጣ ከሚቀመጥበትም መሶብ አንድ ኅብስት ወሰደ፤ እንዲሁም በዘይት የታሸ አንድ ኅብስትና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ በስቡና በቀኝ እግሩ ላይ አኖረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፊት ካለው የቅድስና መሶብ አንድ የቂጣ እንጎቻ፥ አንድም የዘይት እንጀራ፥ አንድም ስስ ቂጣ ወስዶ በስቡና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፊት ካለው ከቂጣው እንጀራ ሌማት አንድ የቂጣ እንጐቻ፥ አንድም የዘይት እንጀራ፥ አንድም ስስ ቂጣ ወስዶ በስቡና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖራቸው። |
ከዚያም በኋላ ስቡንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኩላሊቶች ስባቸውንም፥ ቀኝ ወርቹንም ወሰደ፤