La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ እንዲቀደሱም መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና መቀመጫውን ቀባ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዘይቱም ጥቂት ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውን ከነመገልገያ ዕቃው ሁሉ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳሕኑን ከነማስቀመጫው በዘይት ቀባ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዘይቱም ጥቂት ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ በዚሁ ዐይነት ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ይሆኑ ዘንድ በመሠዊያውና ለእርሱ መገልገያ በተሠሩት ዕቃዎች ሁሉ ላይ እንዲሁም በመታጠቢያው ሳሕንና በሳሕኑ ማስቀመጫ ላይ ረጨ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም ዘንድ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ውን ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ውን ቀባ፤ ድን​ኳ​ኒ​ቱ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደ​ሳ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 8:11
13 Referencias Cruzadas  

ጤዛውም ከተነነ በኋላ፥ በመሬት ላይ ስስ የሆነ ቅርፊት የሚመስል ደቃቅ ነገር በምድረ በዳ መሬት ላይ ታየ።


ሙሴም፦ “ማንም ሰው እስከ ጥዋት ከእርሱ ምንም እንዳያስቀር” አላቸው።


ለማስተስረያ የሚሆን የኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን በየቀኑ ታቀርባለህ፤ በእርሱ ላይ ማስተስረያ በምታደርግበት ጊዜ መሠዊያውንም ታስተሰርይለታልህ፤ ቅዱስም እንዲሆን ትቀባዋለህ።


ሰባት ቀን ለመሠዊያው ማስተስረያ ታደርጋለህ፥ ትቀድሰዋለህም፤ መሠዊያውም ፍጹም ቅዱስ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።


ቀድሳቸው ፍጹም የተቀደሱ ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።


ይህንንም ተአምራት የምታደርግበትን በትር በእጅህ ይዘኸው ትሄዳለህ።”


ጌታም ደግሞ፦ “እጅህን ወደ ብብትህ አስገባ” አለው። እጁንም ወደ ብብቱ አስገባ፤ ባወጣውም ጊዜ፥ እጁ እንደ በረዶ ነጭ እንደሆነ አየ።


ያልተነገረላቸውን ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውኃ እረጫለሁ እናንተም ትነጻላችሁ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።


ካህኑም በግራ እጁ መዳፍ ላይ ያለውን ዘይት በቀኝ ጣቱ ነክሮ ከዘይቱ በጌታ ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል።


ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በጌታ ፊት በመጋረጃው ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።


ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በጌታ ፊት በመቅደሱ መጋረጃ ትዩዩ ደሙን ሰባት ጊዜ ይረጫል።


ይህንንም መንፈስ፥ በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በእኛ ላይ አትረፍርፎ አፈሰሰው፤