ዘሌዋውያን 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይፈኑንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በጌታ ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናል፥ ወይፈኑንም በጌታ ፊት ያርደዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይፈኑን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫን፤ በእግዚአብሔርም ፊት ይረደው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኰርማውንም ወደ ድንኳኑ ደጃፍ አምጥቶ እጁን በእንስሳው ራስ ላይ በመጫን በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይረደው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይፈኑንም ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭነዋል፤ ወይፈኑንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይፈኑንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭነዋል፥ ወይፈኑንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል። |
አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውንም ሁሉ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ያደርገዋል።
ሌዋውያኑም በወይፈኖቹ ራሶች ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ፤ ለሌዋውያንም ማስተስረያ እንዲሆኑ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ አቅርብ።
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።