ዘሌዋውያን 27:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሻውንም ባይቤዠው፥ ወይም ለሌላ ሰው ቢሸጥ፥ እንደገና ሊቤዠው አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕርሻውን ባይዋጅ ወይም ለሌላ ሰው አሳልፎ ቢሸጥ፣ ከዚያ በኋላ ሊዋጀው አይችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞው ባለ ንብረት መሬቱን ከእግዚአብሔር እንደገና ከመዋጀቱ በፊት ለሌላ ሰው ሸጦት ቢገኝ ግን ያንን መሬት እንደገና መልሶ የመዋጀት መብቱን ያጣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻውንም ባይቤዠው፥ ወይም ለሌላ ሰው ቢሸጥ እንደ ገና ይቤዠው ዘንድ አይቻለውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሻውንም ባይቤዠው፥ ወይም ለሌላ ሰው ቢሸጥ፥ እንደገና ይቤዠው ዘንድ አይቻለውም። |