ከዚህ በኋላ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፥ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የሚበቅለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ፤
ዘሌዋውያን 25:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከርህ ማንም ሰው ሳይዘራው የበቀለውን አትሰብስብ፥ ያልተገረዘውን የወይንህን ተክል ፍሬ አታከማች፤ ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ዓመት ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳይዘራ የበቀለውን አትጨደው፤ ካልተገረዘው የወይን ተክልህ ፍሬ አትሰብስብ። ምድሪቱ የአንድ ዓመት ዕረፍት ታድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳይዘራ ገቦ ሆኖ የበቀለውንም እህል አትሰበስብም፤ ካልተገረዘውም የወይን ሐረግ ፍሬውን አትሰበስብም፤ ያ ዓመት ምድሪቱ ፍጹም ዕረፍት የምታደርግበት ጊዜ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድራችሁን ገቦ አትጨደው፤ የተቀደሰውንም የወይንህን ፍሬ አታከማች፤ ለምድሪቱ የዕረፍት ዓመት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድራችሁን የገቦ አትጨደው፥ ያልተቈረጠውንም የወይንህን ፍሬ አታከማች፤ ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ዓመት ይሁን። |
ከዚህ በኋላ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፥ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የሚበቅለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ፤
ይህ ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ ታጭዳላችሁ፤ ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
ያ ኀምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ዓመት ይሆናል፤ በእርሱም አትዝሩ፥ እንዲሁም ማንም ሰው ሳይዘራው የበቀለውን አትሰብስቡ፥ ያልተገረዘውን የወይን ተክል ፍሬ አታከማቹ።
የምድሪቱ ሰንበት ለእናንተ፥ ለአንተም፥ ለወንድ ባርያህም፥ ለሴት ባርያህም፥ ተቀጥሮ ለሚያገለግልህም፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ለመጻተኛም ምግብ ትሰጣችኋለች።