ዘሌዋውያን 25:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድ ባርያና ሴት ባርያ እንዲኖራችሁ ብትፈልጉ ግን በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብ መካከል ወንድና ሴት ባርያዎች ትገዛላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የሚኖሩህ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችህ፣ በዙሪያህ ካሉት አሕዛብ መካከል የገዛሃቸው ባሪያዎች ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአካባቢህ ከሚገኙት አሕዛብ መካከል እንዲኖሩህ የምትፈልጋቸውን ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችህ የሚሆኑትን ልትገዛ ትችላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምን ያህል ወንድ ባሪያና ሴት ባሪያ እንዲኖሩህ ብትፈልግ ግን በዙሪያችሁ ካሉት ከእነርሱ ከአሕዛብ ወንድና ሴት ባያሪያዎችን ግዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድ ባሪያና ሴት ባሪያ መግዛት ብትፈልግ ግን በዙሪያችሁ ካሉት ከእነርሱ ከአሕዛብ ወንድና ሴት ባሪያዎችን ግዙ። |
እንዲሁም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው ከእናንተ ጋር ካሉት ከቤተሰቦቻቸው ውስጥ ባርያዎችን ትገዛላችሁ፤ ርስትም ይሆኑላችኋል።