ዘሌዋውያን 25:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው ባርያዎቼ ናቸውና እንደ ባርያዎች አይሸጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከግብጽ ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ስለ ሆኑ እንደ ባሪያ አይሸጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን የእኔ አገልጋዮች ናቸው፤ እኔ ከግብጽ ምድር ነጻ አውጥቼአቸዋለሁ፤ ስለዚህም ባርያ ሆነው መሸጥ የለባቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎች ናቸውና ባሪያ እንደሚሸጥ አይሸጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸውና እንደ ባሪያዎች አይሸጡ። |
ባርያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ ቀና ብላችሁም እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።”