ዘሌዋውያን 25:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ነፃ ይወጣል፥ ወደ ወገኖቹም ወደ አባቱም ርስት ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ እርሱና ልጆቹ በነጻ ይለቀቁ፤ ወደ ቤተ ሰቡና ወደ አባቶቹ ንብረት ይመለስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ዓመት እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ተለይቶ ወደ ወገኖቹና ወደ አባቶቹ ንብረት ይመለሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢዮቤልዩ ዓመትም እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ይወጣል፤ ወደ ወገኖቹም፥ ወደ አባቱም ርስት ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ይውጣ፥ ወደ ወገኖቹም ወደ አባቱም ርስት ይመለስ። |
ኀምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእንናተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ ከእናንተም እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለሳል።
ለማስመለስ ግን በቂ ገንዘብ ባያገኝ፥ ሽያጩ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዛው ሰው እጅ ይሆናል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይወጣል፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።