ዘሌዋውያን 25:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እስከ ሸጠበት ጊዜ ያሉትን ዓመታት ያሰላል፥ ከዚያም የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልሳል፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስቱን ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሽያጭ ዘመን በመቍጠር የዋጋውን ልዩነት ለገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ገዛ ርስቱ ይመለስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ማድረግ በሚችልበት ጊዜ እስከ ተከታዩ የንብረት መመለስ ዓመት ያለውን ዘመን ቈጥሮ ቀሪውን ገንዘብ ለገዛው ሰው ከመለሰለት በኋላ ወደ ርስቱ ይመለስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሽያጩን ዘመን ቈጥሮ የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሽያጩን ዘመን ቈጥሮ የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ። |
ነገር ግን እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢቀድስ፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ቊጥር ገንዘቡን ያስላልህስ፤ ከዚያም ከግምትህ ላይ ይቀነሳል።