ዘሌዋውያን 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላም ወይም በግ ብትሆን እርሷንና ልጇን በአንድ ቀን አትረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላምን ከጥጃዋ፣ በግንም ከግልገሏ ጋራ በአንድ ቀን አትረዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ላምን ከጥጃዋ ጋር፥ በግንም ከግልገልዋ ጋር በአንድ ቀን አትረድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ብትሆን እርስዋንና ልጅዋን በአንድ ቀን አትረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላም ወይም በግ ብትሆን እርስዋንና ልጅዋን በአንድ ቀን አትረዱ። |
“አንተ ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ እንዲበላ ልትሰጠው ትችላለህ፤ ወይም ለውጭ አገር ሰው ልትሸጠው ትችላለህ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።