ዘሌዋውያን 21:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድንም ወደ አለበት ስፍራ ሁሉ አይሂድ፥ ስለ አባቱም ወይም ስለ እናቱ አይርከስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስከሬን ወዳለበት ስፍራ አይግባ፤ ስለ አባቱም ሆነ ስለ እናቱ ራሱን አያርክስ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማናቸውም ሰው አስከሬን የአባቱም ሆነ ወይም የእናቱ ወደ አለበት ቤት ገብቶ ራሱን አያርክስ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሞተ ሰው ሁሉ አይግባ፤ በአባቱም ወይም በእናቱ አይርከስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ በድንም ሁሉ አይግባ፥ በአባቱም ወይም በእናቱ አይርከስ። |
“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።