ዘሌዋውያን 20:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመዱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ በደላቸውን ይሸከማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከእናትህም ሆነ ከአባትህ እኅት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ የሥጋ ዝምድናን ማቃለል ስለ ሆነ ሁለታችሁም ትጠየቁበታላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአክስትህ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ፤ በዚህ የሥጋ ዝምድናን ማፍረሳቸው ስለ ሆነ ሁለቱም ፍዳቸውን ይቀበላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመድን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመድን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ። |