ዘሌዋውያን 19:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በግብጽ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገሩ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፥ እርሱንም እንደራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱት፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብሯችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ገዛ ወገናችሁ ይታይ፤ እንደ ራሳችሁም ውደዱት፤ እናንተም በግብጽ መጻተኞች ነበራችሁና፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእስራኤላዊ ወገናችሁ በምታደርጉት ዐይነት መልካም ነገር አድርጉላቸው፤ እንደ ራሳችሁም አድርጋችሁ ውደዱአቸው፤ እናንተም ከዚህ በፊት በግብጽ ምድር ባዕዳን እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና፤ ወደ እናንተ የመጣ እንግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁንላችሁ፤ እርሱን እንደ ራሳችሁ ውደዱት፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በግብፅ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገር ልጅ ይሁንላችሁ፥ እርሱንም እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። |
ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጡ በእናንተም መካከል ልጆች ለወለዱ ስደተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትካፈሉአታላችሁ፤ እነርሱም በእስራኤል ልጆች መካከል እንዳሉ የአገር ልጆች ይሆኑላችኋል፥ በእስራኤልም ነገዶች መካከል ከእናንተ ጋር ርስትን ይወርሳሉ።