La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 18:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኅትዋ በሕይወት እስካለች ድረስ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ የእርሷን እኅት እንደ ሁለተኛ ሚስት አድርገህ አታግባ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅቷን ጣውንት አድርገህ አታግባት፤ ከርሷም ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሚስትህ በሕይወት እያለች እኅትዋ ጣውንትዋ እንዳትሆን እኅትዋን አታግባ፤ ከእርስዋም ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ኅቷ ላይ እን​ዳ​ት​ቀና ሚስ​ትህ በሕ​ይ​ወት ሳለች የእ​ኅ​ቷን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሚስትህ በሕይወት ሳለች እኅትዋ ጣውንትዋ እንዳትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ከእርስዋ ጋር እኅትዋን አታግባ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 18:18
8 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብም እንዲህ አደረገ፥ ይህችንም ሳምንት ፈጸመ፥ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ሰጠው።


“የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። እርሷም፦ “ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም፦ “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ” አለች።


ላሜሕም ሁለት ሚስቶችን አገባ፥ የአንዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁለተኛይቱ ስም ጺላ ነበረ።


አምስቱ መጋረጆች እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ፤ አምስቱም መጋረጆች እንዲሁ እርስ በርሳቸው የተጋጠሙ ይሁኑ።


የሴትንና የሴት ልጇን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድ ልጇን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጇን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ እርሷን አታግባ፤ ዘመዶች ናቸው፤ ዝሙት ነው።


“እርሷም ርኩስ በሆነችበት የወር አበባዋ ጊዜያት ላይ ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ ወደ ሴት አትቅረብ።


አንድ አላደረጋቸውምን? የመንፈስም ቅሪት ለእርሱ ነው? አንዱስ ምን ፈልጎ ነው? የእግዚአብሔርን ዘር ፈልጎ ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።