ዘሌዋውያን 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድምህን ሚስት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድምህ ኃፍረተ ሥጋ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከወንድምህ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ ወንድምህን ያዋርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዋርሳ ስለ ሆነች ከወንድምህ ሚስት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድምህን ሚስት ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድምህ ኀፍረተ ሥጋ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህን ሚስት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የወንድምህ ኃፍረተ ሥጋ ነው። |
“መምህር ሆይ፤ የአንድ ሰው ወንድም ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ ይህ ሰው ሴትዮዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር እንዲተካ ሙሴ ጽፎልናል።
ሄሮድስ ራሱ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን በማግባቱ ምክንያት፥ ተይዞ እንዲታሰር ትእዛዝ በመስጠት ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገብቶት ነበር።
“ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።