ዘሌዋውያን 18:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ፤ የእነርሱ ኃፍረተ ሥጋ የአንተ ኃፍረተ ሥጋ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ ይህ አንተን ያዋርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀፍረተ እንዳይሆንብህ ከልጅ ልጅህ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአንተ ኀፍረተ ሥጋ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአንተ ኃፍረተ ሥጋ ነውና። |
የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በአገር ቤት ወይም በውጭ አገር የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።