ዘሌዋውያን 16:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከደሙም በእርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል፥ ከእስራኤልም ልጆች ርኩስነት ያነጻዋል፥ ይቀድሰዋልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእስራኤላውያንም ርኩሰት መሠዊያውን ለማንጻትና ለመቀደስ ከደሙ ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከደሙም ጥቂቱን ወስዶ በጣቱ እየነከረ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ይርጭ፤ በዚህም ዐይነት ከእስራኤል ሕዝብ ርኲሰትን በማንጻት መሠዊያውን የተቀደሰ ያደርገዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደሙም በእርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል፤ ከእስራኤልም ልጆች ርኩስነት ያነጻዋል፤ ይቀድሰውማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደሙም በእርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጫል፥ ከእስራኤልም ልጆች ርኩስነት ያነጻዋል፥ ይቀድሰውማል። |
ከወይፈኑም ደም ወስዶ በስርየቱ መክደኛ ትይዩ በምሥራቅ በኩል በጣቱ ይረጨዋል፤ እንዲሁም ከደሙ በስርየቱ መክደኛ ፊት ለፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጫል።