ዘሌዋውያን 13:59 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑን ለመወሰን እንዲቻል፥ በበግ ጠጉር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ የሚወጣ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከበግ ጠጕር ወይም ከበፍታ የተሠራ ልብስ ወይም በሸማኔ ዕቃ የተሠራ ወይም በእጅ የተጠለፈ ጨርቅ ወይም ከቈዳ የተሠራ ማንኛውም ዕቃ በደዌ ቢበከል፣ ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑን ለማወቅ ሕጉ ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ እንግዲህ ከበፍታም ሆነ ከበግ ጠጒር፥ ወይም ከቈዳ በተሠራ ልብስ ላይ በድሩም ሆነ በማጉ በሻጋታ አማካይነት የሚተላለፍ ምልክት ተመርምሮ የሚታወቅበት የሥርዓት መመሪያ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በበግ ጠጕር ልብስ፥ ወይም በተልባ እግር ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተደረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበግ ጠጕር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛ በተደረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው። |
ነገር ግን አንተ ካጠብኸው ልብስ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ ከተሠራ ከማናቸውም ነገር ላይ ደዌው ቢጠፋ፥ ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል።
“እንዲሁም በመካከላቸው የምትገኘውን የመገናኛዬን ድንኳን በማርከስ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ፥ እናንተ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለዩአቸው።”
እርሷ በብላቴንነትዋ ጊዜ በአባትዋ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል እንዲሆን ጌታ ሙሴን ያዘዘው ሥርዓት ይህ ነው።”