ዘሌዋውያን 13:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ቀን ደዌውን ያያል፤ ደዌውም በልብሱ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በተለፋው ቆዳ ወይም ለማናቸውም አገልግሎት በሚውል የተለፋ ቆዳ ላይ ቢሰፋ፥ ደዌው እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነው፤ እርሱም ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛውም ቀን ይመርምረው፤ ደዌው በልብሱ፣ በሸማኔ ዕቃ በተሠራው ወይም በእጅ በተጠለፈው ጨርቅ ወይም ለማንኛውም አገልግሎት በሚውል ዐጐዛ ላይ ተስፋፍቶ ቢገኝ፣ ክፉ ደዌ ነው፤ ዕቃውም ርኩስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባተኛውም ቀን እንደገና በሚመረምረው ጊዜ ሻጋታው ነገር ተስፋፍቶ ከታየበት ያ የታየው አጥፊ ሻጋታ ስለ ሆነ፥ የዚያ ዐይነቱ ልብስ ሁሉ ርኩስ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባተኛውም ቀን ደዌውን ያያል፤ ደዌውም በልብስ ላይ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በቆዳው ወይም ከቆዳው በሚደረግ ነገር ቢሰፋ፥ ደዌው እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ቀን ደዌውን ያያል፤ ደዌውም በልብስ ላይ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም በአጐዛው ወይም ከአጐዛው በሚደረግ ነገር ቢሰፋ፥ ደዌው እየገፋ የሚሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው። |
ልብሱን ያቃጥል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ወይም ከተለፋው ቆዳ የሆነ ማናቸውም ደዌው ያለበት ነገር ላይ ቢሆን፥ እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነውና በእሳት ይቃጠል።