ዘሌዋውያን 13:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነጻ በኋላ ግን ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጹሕ መሆኑ ከተገለጠ በኋላ ግን የሚያሳክከው ቍስል ተስፋፍቶ ቢገኝ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ንጹሕ መሆኑ ከተገለጠ በኋላ ቊስሉ እያመረቀዘ ተስፋፍቶ ቢገኝ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከነጻ በኋላ ግን ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ያየዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከነጻ በኋላ ግን ቈረቈሩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ያየዋል፤ |
ካህኑ ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ከቆዳው በታች ዘልቆ ቢታይ፥ በውስጡም ቀጭን ብጫ ጠጉር ቢኖርበት፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ቈረቈር ነው፤ የራስ ወይም የአገጭ የለምጽ ደዌ ነው።
ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ባይሰፋ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ ልብሱንም ያጥብና ንጹሕ ይሆናል።