La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 13:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ካህኑም በሰባተኛው ቀን ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ ባይሰፋ፥ በውስጡም ብጫ ጠጉር ባይኖር፥ የቈረቈሩም መልክ ከቆዳው በታች ባይዘልቅ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቍስሉን ይመርምር፤ የሚያሳክከው ቦታ ያልሰፋ፣ ቢጫ ጠጕር የሌለውና ከቈዳው በታች ዘልቆ ያልገባ ከሆነ፣

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሰባተኛው ቀን እንደገና ካህኑ ይመርምረው፤ ቊስሉ እየተስፋፋ ካልሄደ፥ ወደ ቢጫነት የተለወጠ ጠጒርም ከሌለና በዙሪያው ካለው ከሌላው ሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ካልተገኘ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ደዌ​ውን ያያል፤ እነ​ሆም፥ ቈረ​ቈሩ ባይ​ሰፋ፥ በው​ስ​ጡም ብጫ ጠጕር ባይ​ኖር፥ የቈ​ረ​ቈ​ሩም መልክ ወደ ቆዳው ባይ​ጠ​ልቅ፤ ይላ​ጫል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ካህኑም በሰባተኛው ቀን ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ ባይሰፋ፥ በውስጡም ብጫ ጠጕር ባይኖር፥ የቈረቈሩም መልክ ወደ ቁርበቱ ባይጠልቅ፥ ይላጫል፥

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 13:32
6 Referencias Cruzadas  

ካህኑ ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ከቆዳው በታች ዘልቆ ቢታይ፥ በውስጡም ቀጭን ብጫ ጠጉር ቢኖርበት፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ቈረቈር ነው፤ የራስ ወይም የአገጭ የለምጽ ደዌ ነው።


ካህኑም የቈረቈሩን ደዌ ቢያይ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ ጥቁርም ጠጉር ባይኖርበት፥ ካህኑ የቈረቈር ደዌ ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ይለየዋል።


ይላጫል፥ ቈረቈሩ ግን አይላጭም፤ አሁንም ካህኑ ቈረቈር ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ይለየዋል።


ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት ሰው እንዲያይላቸው ነው፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፤


በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታዋርዳለህን?