ዘሌዋውያን 13:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቋቁቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቆዳውም ላይ ባይሰፋ ነገር ግን ቢከስም፥ የቃጠሎው እባጭ ነው፤ የቃጠሎውም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቋቍቻ ባለበት ከቈየና በቈዳው ላይ ካልተስፋፋ፣ ይልቁንም እየከሰመ ከሄደ፣ በቃጠሎው ሰበብ የተከሠተ ዕብጠት ነውና ካህኑ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ የቃጠሎው ጠባሳ እንጂ ሌላ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ቊስሉ ያለበት ስፍራ ምንም ለውጥ ሳያሳይና ሳይስፋፋ የቀለም መለዋወጥ ብቻ ሆኖ ከተገኘ በእሳት ቃጠሎ ምክንያት የመጣ ጠባሳ ስለ ሆነ ያ ሰው ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቋቍቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቆዳውም ላይ ባይሰፋ፥ ነገር ግን ቢከስም፥ የትኩሳት እባጭ ነው፤ የትኩሳትም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍቁቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቁርበቱም ላይ ባይሰፋ ነገር ግን ቢከስም፥ የትኩሳት እባጭ ነው፤ የትኩሳትም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፥ |