ዘሌዋውያን 13:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ካህኑ ቢያየው፥ በቋቁቻውም ላይ ነጭ ጠጉር ባይኖር፥ ከቆዳውም በታች ባይዘልቅ ነገር ግን ቢከስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለየዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ ነጭ ጠጕር የሌለበት፣ ከቈዳውም በታች ዘልቆ ያልገባና የከሰመ ቢሆን፣ ካህኑ ሰውየውን ሰባት ቀን ያግልለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በእርሱ ላይ የበቀለው ጠጒር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ በዙሪያውም ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ካልተገኘና የቀለም መለዋወጥ ብቻ ሆኖ ከተገኘ፥ ካህኑ ያ ሰው ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ቢያየው፥ በቋቍቻውም ነጭ ጠጕር ባይኖር፥ ወደ ቆዳውም ባይጠልቅ፥ ነገር ግን ቢከስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለየዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ቢያየው፥ በቍቁቻውም ነጭ ጠጕር ባይኖር፥ ወደ ቁርበቱም ባይጠልቅ ነገር ግን ቢከስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይዘጋበታል። |
ካህኑ ያየዋል፥ እነሆም፥ በቋቁቻው ላይ ያለው ጠጉር ተለውጦ ቢነጣ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ቢታይ፥ የለምጽ ደዌ ነው፤ ከተቃጠለውም ስፍራ ወጥቶአል፤ ካህኑም፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው።