ዘሌዋውያን 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብጉንጁም የቁስል ስፍራ ላይ ነጭ እባጭ ወይም ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ቋቁቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕባጩ በነበረበት ቦታ ላይም ነጭ ዕብጠት ወይም ነጣ ያለ ቀይ ቋቍቻ ቢታይ፣ ካህኑ ዘንድ ይቅረብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘግየት ብሎም ቊስሉ ባለበት ቦታ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቁቻ ዐይነት ቊስል ቢወጣበት ወደ ካህኑ ይሂድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍስሉም ስፍራ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቋቍቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቍስሉም ስፍራ ነጭ እባጭ ወይም ቀላ ያለ ቍቁቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል። |
ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ቢታይ፥ ጠጉሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የለምጽ ደዌ ነው፤ ከብጉንጁ ቁስል ውስጥ ወጥቶአል።
ካህኑም ያየዋል፤ እነሆም፥ የደዌው እብጠት፥ በሰውነቱ ቆዳ ላይ የሆነ የለምጽ ደዌ መስሎ፥ በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ላይ ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ቢሆን፥