ዘሌዋውያን 13:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም የሚያዠውን ሥጋ አይቶ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የሚያዠው ሥጋ የለምጽ ደዌ ነውና ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም የተገለጠውን ቀይ ሥጋ በሚያይበት ጊዜ ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ፤ ቀይ ሥጋ ርኩስ ስለ ሆነ፣ ተላላፊ በሽታ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም እንደገና መርምሮት የሚያዥ ቊስል ቢያገኝ፥ ያ ሰው የረከሰ መሆኑን ያስታውቅ፤ የሚያዥ፥ የሥጋ ደዌ በሽታ ስለ ሆነ ያ ሰው ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ጤነኛውን ቆዳ አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ ስለዚህ ለምጽ ነውና ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም የሚያዠውን ሥጋ አይቶ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ የሚያዠው ሥጋ ለምጽ ነውና ርኩስ ነው። |