ዘሌዋውያን 11:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሚርመሰመሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታጸይፉ፤ እንዳትረክሱም የገዛ አካላችሁን በእነርሱ አታርክሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚህ ፍጥረታት ሁሉ ራሳችሁን አስጸያፊ አታድርጉ፤ በእነርሱም ራሳችሁን በማጕደፍ አትርከሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነዚህ ውስጥ ማንኛውንም በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ ሰውነታችሁን አታርክሱ፤ በእነርሱም እንዳትረክሱ ሰውነታችሁን አታርክሱባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ ሰውነታችሁን አታስጸይፉ፤ በእነርሱም እንዳትረክሱ ሰውነታችሁን አታርክሱባቸው። |
ስለዚህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ርኩስ ከሆነው ትለያላችሁ፤ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ላይ በሚርመሰመሱ ነፍሳት ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ።