ዘሌዋውያን 11:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ ካለው ዕቃ ውኃ ፈስሶ የሚበላን ምግብ ሁሉ ከነካ ምግቡ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲህም ካለው ዕቃ ሁሉ ማናቸውም የሚጠጣ መጠጥ በውስጡ ካለ እርሱ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም ምግብ እንዲህ ካለው ዕቃ ውሃ ቢፈስስበት ይረክሳል፤ ከዚህ ዕቃ የሚጠጣውም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚበላ ምግብ ሁሉ ከሸክላው ዕቃ የውሃ ነጠብጣብ ቢያርፍበት፥ ርኩስ ይሆናል፤ የሚጠጣም ነገር ቢሆን በዚያ ሸክላ ዕቃ ውስጥ ካለ ርኩስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱ ውስጥ ያለው፤ ውኃም የሚፈስስበት፥ የሚበላ መብል ሁሉ ርኩስ ነው፤ በዚህም ዕቃ ሁሉ ያለው የሚጠጣ መጠጥ ሁሉ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱ ውስጥ ያለው፥ ውኃም የሚፈስስበት የሚበላ መብል ሁሉ ርኩስ ነው፤ በዚህም ዕቃ ሁሉ ያለው የሚጠጣ መጠጥ ሁሉ ርኩስ ነው። |
ለንጹሖች ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ነገር ምንም የለም፤ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው ረክሶአል።