ዘሌዋውያን 11:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰኮናውም የተከፈለ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ያልተሰነጠቀ፥ የሚያመሰኳም እንሰሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ እርሱንም የሚነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ሰኰና ያለው፣ ነገር ግን ሰኰናው ያልተሰነጠቀና የማያመሰኳ ማንኛውም እንስሳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን። የእነዚህንም በድን የሚነካ ሰው ሁሉ ይረክሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰኰና ያለው፥ ነገር ግን ሰኰናው በሙሉ ያልተሰነጠቀና የማያመሰኩ እንስሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱን የሚነካ ሁሉ ይረክሳል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰኰናም ያለው፥ ነገር ግን ሰኰናው ያልተሰነጠቀ፥ የማያመሰኳም እንስሳ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ እርሱን የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰኮናም ያለው፥ ነገር ግን ሰኮናው ያልተሰነጠቀ፥ የሚያመሰኳም እንሰሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ እርሱንም የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው። |
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ መካከል፥ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ዐሣማም፥ ምንም እንኳ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩህ፥ እርሱ ለእናንተ ንጹሕ አይደለም፤ የእነዚህን ሥጋ አትብሉ፤ ጥምባቸውንም አትንኩ።