ዘሌዋውያን 11:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሌሎች አራት እግሮች ያሉአቸው ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረታት ተጸየፏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሌሎች ክንፎችና አራት እግሮች ያሉአቸው ፍጥረቶች እንደ ርኩስ ይቈጠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚበርር፥ አራትም እግሮች ያሉት ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የሚበርር፥ አራትም እግሮች ያሉት ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው። |
ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ፤ አንበጣዎችን በየወገናቸው፥ ደጎብያዎችን በየወገናቸው፥ ፌንጣዎችን በየወገናቸው፥ ኲብኲባዎችን በየወገናቸው።
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ መካከል፥ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።