አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
ዘሌዋውያን 11:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በአራት እግሮች የሚንቀሳቀሱ፥ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ክንፍ ያላቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ የረከሱ ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሚበርርም፥ በአራት እግሮችም የሚሄድ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚበርርም፥ በአራት እግሮችም የሚሄድ ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው። |
አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
ነገር ግን ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው፥ በአራት እግሮች ከሚሄዱ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት እነዚህን ትበላላችሁ።
በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ መካከል፥ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”