ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ።
ከሞቱ ብዙ ጊዜ እንደ ሆናቸው፣ በጨለማ እንድኖር አደረገኝ።
ከብዙ ጊዜ በፊት እንደ ሞተ ሰው በጨለማ ውስጥ እንድቀመጥ አስገደደኝ።
እንደ ቀድሞ ሙታን በጨለማ አኖረኝ።
ጠላት ነፍሴን አሳድዶአታል፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ አጐስቁሎአታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨለማ አኑሮኛል።
አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።
እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዐይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።