ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
ሰው በወጣትነቱ፣ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
ሰው በወጣትነቱ መከራን በትዕግሥት ቢቀበል መልካም ነው።
ሰው በታናሽነቱ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው።
ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።
በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኖቻችንን እንዴት እንደምንቆጥር እንዲህ አስታውቀን።
ለክፉ ሰው ጉድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከአስከፊ ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።
የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፥ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፥
ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
ዮድ። እርሱ አሸክሞታልና ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ።