ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ።
ሆኖም ይህን ዐስባለሁ፤ እንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤
ሆኖም ይህን አንድ ነገር በማስብበት ጊዜ በተስፋ እሞላለሁ።
ይህችን በልቤ አኖራለሁ፤ ስለዚህ እታገሣለሁ።
ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፥ በቃልህም ታመንሁ።
ከጌታ ጋር ጽኑ ፍቅር፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን አለና እስራኤል በጌታ ይታመን።
ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና።
ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይፈጥናል፥ እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ጠብቀው፤ አይዘገይም።