ዮዲት በነበረችበት ጊዜና ከሞተችም በኋላ ለብዙ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች የሚያስፈራ ማንም አልነበረም።
ከእነዚያም ወራት በኋላ ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ተመለሰ፤ ዮዲትም ወደ ቤጤልዋ ተመልሳ በንብረቷ ኖረች፤ በዘመኗም በሀገሩ ሁሉ የከበረች ሆነች።